ኢዲአር ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡ ****

  • Post author:
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:3 mins read

ኢዲአር ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡ ****

መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢዲአር)፡- የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ (ኢዲአር) ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በትብብር መስራት የሚስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የኢዲአር ዋና ስራ አስፈፃሚ አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) እና የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩብ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ናቸው፡፡ በስምምነቱ መሰረት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለባቡር መሠረተ ልማት ግብአት የሚሆኑ የተለያዩ የብረታ ብረት፣ ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም የፕላስቲክ ምርቶችን እንደሚያቀርብ ተገልጿል፡፡ ስምምነቱ ተግባራዊ ሲሆን ኢዲአር የሚያጋጥሙትን የባቡር መሠረተ ልማት መለዋወጫ ዕቃዎች እጥረት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቅርፍ ተመላክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኢዲአር በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ለመለዋወጫ ግዢ የሚያወጣውን የውጪ ምንዛሬ ማዳን ያስችላል ተብሏል፡፡ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኢንዱስትሪዎች የሆኑት አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ፣የፓወር ኢኩመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪና የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪዎች  እነዚህን የባቡር መሠረተ ልማት መለዋወጫ ዕቃዎች እንደሚያመርቱ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ገልፀዋል፡፡ ኢዲአር እየሰጠ የሚገኘውን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በባቡር መሠረተ ልማት መለዋወጫ እጥረት ምክንያት ክፍተት እንዳይፈጠር ለማድረግ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የሚያቀርበው የተለያዩ መለዋወጫዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲሚያበረክቱ የኢዲአር ዋና ስራ አስፈፃሚ አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡ በመግባቢያ ሰነዱ መሠረት በአስቸኳይ የጋራ የቴክኒክ ግብረ ሀይል በማቋቋምንና ዝርዝር ተግባራትን በመለየት ወደ ተግባር መግባት የሚያስችሉ ነጥቦችን ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ  ተቋማቱ በጋራ የሚሯቸውን ስትራቴጂያዊ ስራዎች በፍጥነትና በጥልቀት ለይቶ በማቅረብ ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግ እንደሚገባ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
Facebook
Twitter
LinkedIn

Leave a Reply