Skip to content
ጥቅምት 05 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢዲአር)፦የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ አመራርና ሠራተኞች ከፌዴራል ፖሊስ የባቡር ዲቪዥን አባላት ጋር በመሆን 16ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ፉሪ ለቡ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ቅጥር ጊቢ አከበሩ።
‘የሰንደቅ አላማችን ከፍታ ለህብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው’ በሚል መሪ ቃል በተከበረው መርሃግብር ላይ የተገኙት የኢዲአር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የሎጂስቲክስና ፕሮኪውርመንት ቺፍ ኦፊሰር ሄኖክ ቦጋለ እንዳሉት ሰንደቅ ዓላማችን የብዝኃነታችንና የኅብረ ብሔራዊነታችን መገለጫና የአብሮነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና ነፃነታችን ምልክት ነው። በትውልድ ቅብብሎሽ ሰንደቅ አላማችን ከፍ ብላ እንድትውለበለብ በማድረግ ረገድ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ የፌዴራል ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት ለከፈሉት መስዋዕትነ ልዩ ክብር አለን ብለዋል።
የፌዴራል ፖሊስ የባቡር ዲቪዥን አባላት ወታደራዊ ትርዒት በማከናወንና በሰንደቅ አላማችን ፊት በመሆን የሀገራችን ክብርና ነጻነት በመበቅና በማስጠበቅ እያከናወኑ ያለውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት ዳግም ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ህዝብ መዝሙር በመዘመርና የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።