ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢዲአር)፦ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለ4ኛ ጊዜ የተዘጋጀውን አውደርእይ የኢዲአር አመራርና ሠራተኞች ጎብኝተዋል።
በኢዲአር የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት አስተባባሪነት የተከናወነው ጉብኝት ላይ ስለሳይበር ደህንነት ምንነት አጠቃላይ መረጃ የተሰጠ ሲሆን ሀገራችን የደረሰችበትን የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶች የተመለከቱ ገለፃዎች ተሰጥቷል።
ለግብርና አገለግሎት፣ የህክምና ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚረዱና፣ ለወታደራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ድሮኖችና መሠል የቴክኖሎጂ ውጤቶች በአውደርዕዩ ተካተዋል።