ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢዲአር)፡- የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ ከብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ሃሳብ የተከበረውን 116ኛውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ መርሃግብር አከናውኗል፡፡
ፉሪ ለቡ በሚገኘው የኢዲአር ዋ መስሪያ ቤት በተከናወነው የደም ልገሳ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ደም በመለገስ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት አረጋግጠዋል፡፡
ደም የለገሱ አመራሮችና ሰራተኞች በዚህ ወቅት እንዳሉት በዘመናት ቅብብሎሽ ከቀደምቶቹ የወረሰውን ጀግንነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ እየተጋ ለሚገኘው ኀብረ ብሔራዊ ሠራዊት ያለንን ክብር ደም በመለገስ እንገልፃለን ብለዋል፡፡
የማይተካ ህይወቱን በመስጠት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ ለሚያፀናውና የኢትዮጵያዊነታችን የመጨረሻ ምሽግ ከሆነው ሠራዊታችን ጎን ሁሌም እንቆማለን ብለዋል፡፡