ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢዲአር)፦ ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ የሎኮሞቲቭ እና ሮሊንግ ስቶክ (locomotive and rolling stock) የስራክፍል ሰራተኞች እና አመራሮች በሸገር ከተማ አስተዳደር እንዶዴ አካባቢ የሚገኙ አርሶአደሮችን የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል ።
በዚህ ወቅት የሎኮሞቲቭ እና ሮሊንግ ስቶክ ዳይሬክተር አቶ ተክሌ አባዲ እንደተናገሩት ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ እንደመሆኑ መጠን ሰብላቸውን ለመሰብሰብ በመረባረብ ላይ የሚገኙ አርሶአደሮችን በማገዝ ሰብሉ ያለምንም እንከን እንዲሰበሰብ ለማድረግ ከጎናቸው ለመሆን መገኘታቸውን ተናግረዋል።
አቶ ተክሌ አክለውም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሰብሉን ከማበላሸቱ በፊት ካለን የተጣበበ የስራ ሰዓት በመቀነስ የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብና በማገዝ ከብክነት እና ካላሰፈላጊ ወጪ ለማዳን አጋርነታቸውን እንዳሳዩ ጠቁመው በቀጣይም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በሌሎችም ማህበራዊ አገልግሎቶች ዙሪያ ከጎናቸው እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
ሰብል የተሰበሰበላቸው አርሶአደሮች በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው የባቡር አገልግሎቱን ሁሌም እንደ አይን ብሌናችን የምናየውና የምንከባከበው ከመሆኑ ባሻገር ለአካባቢው ነዋሪ ድጋፍ በማድረግና እንደዚህ የደረሰ አዝመራችንን ለመሰብሰብ ከጎናችን በመሆን ላደረጋችሁልን ድጋፍ ደሰታችን ወደር የለውም ብለዋል።
l