መልካም ዜና ለኢንዱስትሪ ፓርክ አምራቾች በሙሉ
የኢትዮጵያ መንግስት የኮቪድ-19 ወረርሺኝ በሃገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስእየወሰዳቸው የሚገኙ እርምጃዎችን ለመደገፍ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ/ማህበር ከእ.ኤ.አ ሜይ 1/2020 ጀምሮ ለሶስት ወራት ለሚቆይ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለሚገኙ አምራቾች የነፃ የኤክስፖርት ኮንቴይነር ማጓጓዝ አገልግሎት መስጠት መወሰኑን ስንገልጽ በደስታ ነው፡፡ የነፃ ትራንስፖርት አገልግሎቱ ከሞጆ ደረቅ ወደብ እስከ ጅቡቲ ወደብ ድረስ የሚሰጥ ሲሆን፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ አምራቾች በሙሉ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑና ወረርሺኙ በሃገራችን ኢኮኖሚ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ በጋራ እንድንከላከል አ/ማህበሩ ጥሪ ያቀርባል፡፡